የዜማ ትምህርት አሰጣጡ በሚከተለው መልኩ ነው፡፡
- ውዳሴ ማርያም ዜማ
- መስተጋብእ
- ጾመ ድጋ
- አርባዕት
- አርያም
- ሰለስት
- ጾመ ምዕራፍ
መስተጋብእ ። መስተጋብእም ማለት እስትጉቡእ ስብስብ) የተከማቸ ማለት ነው፤ ይኸ. ውም ከዳዊት መዝሙር ከ፩፻፶ው ውስጥ ከየዕለቱ ለጸሎትና ለዝማሬ ተስማሚ የሆነው እየተውጣጣ ለመዝሙር ተስማሚ የሆነ የተቀመረ ነው። ይዚህ ዜማ ደራሲ ቅዱስ ያሬድ ነው። እርሱም መስተጋብእን ሲጀምር "ወለቡ ጸራኅየ" ጩኸቴን ልብ አድርግ ብሎ ይጀምራል።