የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የአብነት ትምህርት ቤት

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ደበሎ የአብነት ትምህርት ቤት በኢንተርኔት

የአብነትትምህርት ቤት ማለት ከአባት የተገኘ ከአበው የተወረሰ ከጥንትየነበረ የማንነት መገለጫ በራስ ቋንቋ በራስ ፊደል በራስ ሥርዐተ ትምህርት የሚሰጥ ከትውልድ ወደ ትውልድ የተላለፈ ትምህርት የሚሰጥበት ትምህርት ቤት ማለት ነው ። የአንድን ሕዝብ የአንድን ሀገር ጥበብ እና ዕውቀት ለዚያሕዝብ እና ለዚያች ሀገር ዜጎች የሚያስተምሩበት ትምህርት ቤት ማለት ነው ። ሥርዐተ ትምህርቱ አገር በቀል በሆኑ ብሔራውያንሊቃውንት ተዘጋጅቷል ። ከጊዜ ወደ ጊዜም ዳብሯል ። የአብነት ትምህርት ቤት በልማድ "የቆሎትምህርት ቤት " በመባል በሕዝባችን ዘንድ ይታወቃል ። አንዳንድ ሰዎች ደግሞ "የቄስ ትምህርት ቤት " እንዲሁም አንዳንዶች " የቤተ ክህነት ትምህርት ቤት " ይሉታል ።የመጀመሪያው ልማዳዊ ስያሜ የተማሪዎቹን አመጋገብና የችግር ኑሮ የሚገልጥ እንጅ የትምህርት ቤቱን ማንነት እና ዓላማ የማያሳይ በመሆኑ ተቀባይነት ያለው ስያሜ አይደለም ። ሌሎቹ ስያሜዎችግን የጥንታዊው ትምህርት ባለቤቶች የሥርዐተ ትምህርቱም ቀራጮች መምህራኑም የቤተ ክርስቲያን ሰዎች በመሆናቸው የሚመሳሰልስያሜ ነው ። የሃይማኖት አባቶች የጥንታዊ ሥልጣኔ መነሻዎች የዘመናዊ ትምህርትም መሠረቶች መሆናቸው በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በሌሎችም ዓለማት ታሪክ የታወቀ ነው ። ያምሆነ ይህ ትክክለኛው ስያሜ "የአብነት ትምህርት ቤት " ነው ። የአብነት ትምህርትቤት የአንድን ሀገር ጥንታዊ ሥነ ጥበብ ሥነ ፊደል ሥነ ዜማ ሥነ ባሕል ሥነ ሥርዐት ሃይማኖት ታሪክ ለዛ ዝዬ ወግ እና ማዕርግ በልዩ ልዩ አቀራረብ አገር በቀል በሆኑ ሊቃውንትበአገር ቋንቋ በሀገር ፊደል አገር በቀል በሆነ የአስተምህሮ ስልት የሚያቀርብ እና የሚሰጥ የትምህርት ቤት ነው ። የአብነት ትምህርት ዓለም አቀፋዊ ዕውቀትንየሚያንጸባርቅ ዓለም አቀፍ ይዘት ያላቸውን ትምህርቶች በሀገራዊ ደረጃ የሚያቀርብ ትምህርት ቤት ነው ። ትምህርቱምለዜጎችም ለውጭ ሀገር ስዎችም ይሰጣል ። በሀገር ውስጥ አእላፍ ሊቃውንትን እንዲሁም ብዙ የውጭ ሀገር ሊቃውንት አፍርቷል ።

በአብነት ትምህርት ቤት የሚሰጡየትምህርት አይነቶች

በአብነትትምህርት ቤት የሚሰጡ የትምህርት አይነቶች የአንድን ሕዝብ ሁለንተናዊ የዕውቀት ዘርፎች ያካትታል ። በሀገራችን የአብነትትምህርት ቤቶች ከሚሰጡት ትምህርቶች ዋና ዋናዎቹ ከዚህ የሚከተሉት ናቸው ።
፩. የፊደል እና የንባብትምህርት ቤት

በዚህ ትምህርትቤት ፊደል ንባብ ዳዊት እና የመጀመሪያ ደረጃ የዜማ ትምህርት ይሰጣል ። ይህም የንባብ እና የጽሑፍ መነሻ የሚሆን መሠረተ ትምህርትነው ። ይህም ትምህርት ቤት ፊደል ከማስቆጠር ስለሚጀምር "የቁጥር የንባብ ትምህርት ቤት" እየተባለም ይጠራል ።


፪. የቋንቋ ትምህርት ቤት

በቅኔ ቤትግዕዝ ከነአገባቡ ይሰጣል ግዕዙን ወደ አማርኛ በመተርጎም ግዕዝን እና አማርኛን አስተባብረውና አዛምደው ያስተምራሉ ። ይህም ትምህርትሥነ ጽሑፍን አገባብን ንባብን ምሳሌአዊ አነጋገርን እና የንግግር ችሎታን ማሳወቅን ያካትታል ።


፫. የዜማ ቤት

በዜማ ቤት ከውዳሴማርያም ዜማ ጀምሮ በመስተጋብዑ በአርባዕቱ በሠለስቱ በጾመ ድጓው በድጓው በዝማሬና መዋስዕቱ በአቋቋሙ በቅዳሴው እና በሌሎችም ከዜማጋር የተያያዙ ትምህርቶች ኢትዮጵያዊ ዜማ ለማደግ ችሏል ። የዚህም ትምህርት አባት ቅዱስ ያሬድ ነው ። ይህም የደስታና የኀዘንጊዜ ዜማዎችን መዝሙርን ማኅሌትን ዘፈንን ወየታን ምሥጋናን እንጉሩጉሮን እና ሌሎችንም ከዜማ ጋር የተያያዙ ባሕላዊ እናሃይማኖታዊ የዜማ ቅኝቶች ሁሉ ያካትታል ።


፬. የቅኔ ቤት

በቅኔ ቤትየፈጠራ ችሎታ (creativity) ወቅታዊ ሁኔታዎችን የመረዳት ችሎታ (perspective and understanding) የአእምሮንጥበብሕ ግን ተከትሎና ቋንቋን መርጦ አጋኖ ወይም አዋርዶ እንዲሁም መካከለኛ ደረጃ ሰጥቶ ሁኔታዎችን የመግለጥ ችሎታ ታሪክንእና ወቅታዊ ሁኔታዎችን አገናዝቦ የማቅረብ ችሎታ ፍልስፍና የአስተሳሰብ ችሎታ ትምህርት (critical thinking) ይሰጥበታል። የቅኔን ባሕርይ እና የአሰጣጥ ስልት ልብ ብሎ ላስተዋለው ከላይ የዘረዘርኩአቸውን እና ሌሎችንም ጥበቦች በቀጥታም ሆነበተዘዋዋሪ ያጠቃልላል ። ከዚህ በተጨማሪ ቅኔ በመቶዎች የሚቆጠሩ መንገዶች ያሉት በመሆኑ እንደየ መንገዱ ልዩ ልዩ የአቀራረብስልትን እና የቋንቋን አገባባዊ መዋቅርን እና ቋንቋዊ ሙያን ለመማር ያስችላል ፡፡


፭. የትርጓሜ ቤት

በዚህ ትምህርትቤት የቅዱሳት መጻሕፍት ትርጓሜ ይሰጥበታል ። ይህም ትምህርት ዓለም አቀፍ ይዘት ያለው ብሔራዊ በሆነ መልኩ የቀረበ የኢትዮጵያንሊቃውንት ዕውቀት ደረጃና ጥንታዊ አስተምህሮ የሚያስረዳ የአብነት ትምህርት ቤት ነው ። ይህ ትምህርት ቤት በሀገራችን ጥንታዊሥርዐተ ትምህርት ከፍተኛው የነገረ መለኮት ትምህርት ቤት ነው በአሁኑ ሰዓት ይህ የትርጓሜ ትምህርት ቤት በአራት ይከፈላልየብሉይ ኪዳን የትርጓሜ ትምህርት ቤት የሐዲስ ኪዳን የትርጓሜ ትምህርት ቤት የመጽሐፈ ሊቃውንት የትርጓሜ ትምህርት ቤትየመጽሐፈ መነኮሳት የትርጓሜ ትምህርት ቤት ።


፮. የቁጥር ትምህርት ቤት

የሂሣብትምህርት በረቀቀ ሁኔታ ይሰጥበት የነበር የአብነት ትምህርት ቤት ነው ። ይህ ትምህርት ቤት የስነ ከዋክብት ትምህርት ሚጠተ ብርሃናት(የብርሃናት ምልልስ) የዘመን አቆጣጠር ትምህርት የሚሰጥበት ትምህርት ቤት ነው ። ዛሬ ግን ከሌሎች የአብነት ትምህርት ቤቶችይልቅ ይህ የአብነት ትምህርት ቤት ተዳክሞ መምህራኑ ጠፍተዋል ጥበቡም ደብዝዟል ። ትምህርቱን ያውቁት የነበሩት የጥንትሊቃውንትም አልቀዋል ርዝራዡ ሳይጠፋ ይህን ጊዜ በዚህ ሙያ ዙሪያ ዕውቀት ያላቸውን ሊቃውንት በማሰባሰብ እና ጥንታውያን የቁጥርመጻሕፍትን በመመርመር ትንሣኤ እንዲያገኝ ካልተደረገ ወደ ትውልድ ሳያልፍ ትልቁ ጥበብ መቅረቱ ነው ። ይህም ለሀገራችን እናዕውቀትን ጥበብን ለሚራቡ ሁሉ ትልቅ ጉዳት ነው ። ከላይበተዘረዘሩት የአብነት ትምህርት ቤቶች የኢትዮጵያውያን ጥንታዊ አስተምህሮ ሃይማኖት ትውፊት ስርዓት ወግ ልማድ ቋንቋ ሥነ ጽሑፍዜማ ትርጓሜ መጻሕፍት፥ ሥርዐተ ማኅሌት ክብርና ታሪክ ከትውልድ ወደ ትውልድ መተላለፍ ችለዋል ። የኢትዮጵያኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በመላ ሀገሪቱ በሚገኙ የአብነት ትምህርት ቤቶች ይልቁንም በጎንደር በጎጃም በሰሜን ሸዋበትግራይ በዋድላ በደላንታ እና በላስታ በወሎ በሚገኙት የአብነት ትምህርት ቤቶች ዕውቀትን የሚራቡትን በመመገብ በኢትዮጵያአብነትነት ያለው አንቱ የሚያስኝ ትምህርት እንዲስፋፋ በማድረግ ታላቅ በረከትን ለትውልዱ አበርክታለች ። ይልቁንም ጎጃምናጎንደር እስከ ዛሬ ድረስ የሀገሪቱ ዋና የአብነት ትምህርት ማዕከላት ናቸው ። ይህንንበተመለክተ ሊቀ ጠበብት አክሊለ ብርሃን ወልደ ቂርቆስ የሚባሉ ሊቅ "መርሐ ልቡና " በተባለው መጽሐፋቸው እንዲህሲሉ ጽፈዋል ። “ ከኢትዮጵያም ጎጃም እና ስመ ጥሩውን ጎንደርን በጣም ማመስገን ይገባናል ። አውሮፓውያን የሊቃውንትን ትምህርትቤት ዩኒሸርሲቲ እንደ ሚሉት ጎንደርና ጎጃምም እንደዚሁ በኢትዮጵያ መንፈሳዊ ትምህርት ቤት ዩኒሸርሲቲ መሆናቸው የታወቀ ነው ።ጎንደር በሐዲስ መጽሐፍና በሊቃውንት መጽሐፍ በዜማ ባሕልና ሥርዐት በማናቸውም በኩል አብነት መባል ይገባዋል ። ጎጃምም እንደዚሁበመጻሕፍተ ብሉያትና በቅኔ በጥንታዊ ባሕልና ታሪክ በኩል ምስክር መባል አለበት ። ስለዚህም ሁለቱ ሀገሮች ዩንሽርሲቲ መባልይገባቸዋል ። ከሁሉም ይልቅ የሚያስደንቅ እነዚህ ሁለቱ ሀገሮች ከሁሉም አውራጃዎች የትምህርትን ማዕድ ለመሳተፍ የመጡትን በብዙሺህ የሚቆጠሩትን ተማሪዎች አስፈላጊውን ትምህርት ጨርሰው እስኪመለሱ ድረስ እስከ ሃያ ወይም እስከ ሰላሳ ዘመን ድረስ ቢቀመጡ፣የሀገሩ ተወላጆች ምዕመናን ምግባቸውን ያለማቋረጥ ስለሚመግቧቸው እና ለመምህራንም ዋጋ መክፈል ስለሌለባቸው ምኞቱን ከፍጻሜየማያደርስ ተማሪ አይገኝም። ከላይ የተጠቀሱት ሁለቱ ሀገሮች መንደሩን እየከፈሉ ስለሚሰጧቸው ተማሪዎች ያለ ሀሳብ ትምህርታቸውንለመቀጠል በምግብ እና በማናቸውም ረገድ አሳብ የለባቸውም ። ስለዚህ በተማሪዎች አኳኋዋን ጎጃምና ጎንደር ዋድላና ላስታ የእናትየአባት ቤት መባል ይገባቸዋል

ለኅብረተሰቡ ያበረከቱት አገልግሎት

የአብነት ትምህርት ቤቶች ለቤተ መንግሥት እና ለኅብረተሰቡ ያበረከቱት አገልግሎት

በአብነትትምህርት ቤቶች የሚሰጠውን ትምህርት የተማሩ የኢትዮጵያ ነገሥታት ክርስቲያኖችነበሩ አናዳንዶቹም ካህናት ነበሩ ። ስለዚህ ቤተ ክርስቲያኒቱ ከአብራኳ የተከፈሉት ነገሥታት ሕዝባቸውን የሚመሩበትን ሕግና ጥበብ ታስተምር ነበር ። በመሆኑም የሕግ ትምህርት በመደበኛነት ይሰጥ ነበር ። መምህራንም የነገዎቹን የሀገር መሪዎችየዛሬዎቹን ደቀ መዛሙርቶቻቸውንበሃይማኖት እና በፈሪሃ እግዚአብሔር በሕግና በሥርዐትእንዲያስዳድሩ ያሰለጥኑአቸው ነበር ። ለምሳሌ አባ ኢየሱስ ሞዐ የአፄይኩኖ አምላክ መምህር ነበሩ ። ሌሎችም በዛጉዬ ዘመነ መንግሥት የነበሩ ነገሥታት ላሊበላን ጨምሮ ካህናት ነበሩ ባክሱም ዘመነ መንግሥትም የነበሩት እነ አጤ ገብረ መስቀል ፍጹም መንፈሳውያን ነበሩ ። በጎንደሮች ዘመነ መንግሥትም እነ አጤ ኢያሱ አድያም ሰገድ ካህናት ነበሩ ። የቅኔ ዘራፊዎች ሊቃውንትም የነበሩ ነገሥታት እንደነበሩ ታሪካችን ይመሰክራል፡፡ ለምሳሌ አፄ በእደ ማርያም አፄ በካፋ የቤተ መንግሥቱ የፍርድ ቤት ዳኞች የነበሩትም የቤተ ክርስቲያኒቱ የሕግና የስርዓትሊቃውንት የነበሩ ናቸው ። በዚህ ትምህርት ቤትሃይማኖት፥ ትውፊት ስርዐት ወግ ልማድ ቋንቋ ሥነ ጽሑፍ ዜማ ትርጓሜ መጻሕፍት ሥርዐተማኅሌት ክብር እና ታሪክ ከትውልድ ወደ ትውልድ መተላለፍ ችለዋል ። በአፍሪካ ብቸኛየሆነው የግዕዝ ፊደል ከነሙሉ ጥበቡ የተረፈው በዚሁ ትምህርት ቤት ነው ።አሁን ከዚህ ላይ ልገልጸው ጊዜና ቦታ ባይፈቅድልኝምየኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የአብነት ትምህርት ቤቶች አስተዋጽኦ ለኢትዮጵያሕዝብና ለኢትዮጵያ መንግሥት ሁለገብና ብሔራዊ ፋይዳ ያለው መሆኑ የታወቀ ነው ። ከዚህ ቀጥሎ በእነዚህ የአብነት ትምህርት ቤቶች የሚሰጡትን ዋና ዋና ትምህርቶች ደረጃ እየሰጠን እናቀርባለን ።

የአንደኛ ደረጃ ትምህርት

ፊደል አቡጊዳ መልእክተ ዮሐንስ የአነባበብ ስልት ትምህርትንባብ (ማጋዝ ውርድ ንባብ ቁም ንባብ) ቀን ቀን ሲሰጡ ሌሊት ሌሊት ደግሞ የቃል ትምህርት ይሰጣል ። ይሄውም የዘወትር ጸሎትውዳሴ ማርያም አንቀጸ ብርሃን መልክዓ ማርያም መልክዓ ኢየሱስ እና ውዳሴ ማርያም ዜማ ናቸው ። ከዚህ በኋላ ቀን ቀን ንባቡንአቀላጥፎ ካነበበ በኋላ ዳዊት ይጀምራል ። ዳዊቱን ተምሮ ሲጨርስ የአንደኛ ደረጃ ትምህርቱን እንዳጠናቀቀ ወደ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤትም እንዳለፈ ይቆጠራል ። ከዚያ በኋላ ትምህርቱን በቀን ብቻ ሳይሆን በሌሊትም አጠናክሮይቀጥላል ። የሌሊቱ ትምህርት የቃል ትምህርት ሲሆን በቃል የሚጠና በአእምሮ የሚወሰን ሲሆን በቀን የሚሰጠው ትምህርት ደግሞ በመጽሐፍየሚጠና ነው ። ስለዚህ በዚህ ጸሐፊ አስተያየት ከአንደኛ ደረጃ ትምህርት ጋራ ሊነጻጸር የሚችለው ሌሊት የሚሰጠው ከቃልትምህርት ከዘወትር ጸሎት እስከ መልክዓ ኢየሱስ ያለው በቀን ከሚሰጠው ትምህርት ደግሞ ፊደልን አቡጊዳን (የፊደል አካል ነው)መልእክተ ዮሐንስን ተምሮ ከዚያ በኋላ የግዕዝ ንባብ በሚማርበት መጽሐፍ ግእዝ ውርድ ንባብ ቁም ንባብ አውቆ ዳዊት ተምሮሲያጠናቅቅ ነው ።

ንባብ

ይህ ደግሞ ተማሪው መምህሩ ንባብ በሚያስተምርበትየግዕዝ መጽሐፍ መጀመሪያ በግዕዝ የአነባበብ ስልት ሁለተኛ በውርድ ንባብ የአነባበብ ስልት (ተነሺ እና ተጣይን ለመለየት በጣምጠቃሚ የሆነ የአስተምሮ ስልት ነው) ከዚያም በመጨረሻም በቁም ንባብ (መደበኛው የግዕዝ መጻሕፍት የሚነበቡበት የአነባበብ ስልትቁም ንባብ ይባላል) ንባብ ይማራል ። ከዚህ ሁሉ በኋላ ተማሪው ዳዊት ይማራል ። ዳዊትም የሚማረው በሁለት የአነባበብ ስልት ነው። አንደኛ በዕዝል ሁለተኛ በቁም ንባብ ይማረዋል ። በዚህ መልኩ ከፊደል እስከ ዳዊት አጠናቆ የተማረ ተማሪ ዳዊት ሲደግምማለት ዳዊት ተምሮ ሲጨርስ (አንድ መቶ ሃምሳውን መዝሙረ ዳዊት ነቢያትን እና መኃልየ ሰሎሞንን ያጠቃልላል) በከፍተኛ ሁኔታይደሰታል ። አንዳንድ ቤተሰቦች ለልጆቻቸው አስተማሪዎች ለዚህ ደረጃ ስላደረሱላቸው የደስታ ስጦታም ያበረክታሉ ። ይህ ተማሪአንደኛ ደረጃ ትምህርቱን ያጠናቀቀ ተማሪን ይመስላል ።

የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት

በቃል ትምህርት በኩል ውዳሴ ማርያም ዜማ መስተጋብዕግብረ ዲቁና ሰዓታት አርባዕት ተምሮ ለዲቁና እና ለቅስና የሚያበቃውን የቃል ትምህርት ሲጨርስ ከፍተኛ ሁለተኛ ትምህርቱን ያጠናቀቀተማሪን ይመስላል ። ለሥራ የሚያበቃ ሁለገብ የሆነ እውቀት ገብይቷልና ። በቀኑ ትምህርት በኩል ደግሞ ቅኔ ተቀኝቶ ለራሱ ያክልሲያውቅ ሩቅና ቅርብ አንድና ብዙ ወንድና ሴት ለይቶ የመጻሕፍትን ሐሣብ ተረድቶ ሌሎችን ለማስረዳት ከሚያስችል ደረጃ ሲደርስከአንድ ማሠልጠኛ ገብቶ ለሥራ የሚያበቃ ሥልጠና አግኝቶ መረጃ ይዞ የወጣ ተማሪን ይመስላል ። ይህ ደረጃ ከመጀመሪያ ድግሪጋርም ሊነጻጸር ይችላል ። እንደ እውነቱ ከሆነ በድካም ደረጃ ከፍተኛ ድካም ነውተማሪው የሚደክመው ። ነገር ግን ዘመናዊው ትምህርት ልዩ ልዩ የትምህርት ዓይነቶችን ያካተተ እና በተቀላጠፈ መልኩ የሚሰጥበመሆኑ በእውቀት ደረጃው ሊመሳሰል ይችላል ።

ዲግሪ

አንድ ሰው ከዚህ ሁሉ ጋር አቋቋም ለራሱ አውቆና ራሱንችሎ ለመቆም የሚያስችል እውቀት ካለው ዜማና ቅኔም ለራሱ ያክል በሚገባ ከወቀ ከማስትሬት ዲግሪ ጋር እኩያ ሊሆን ይችላል ።

ፒ ኤች ዲ

በቤተ ክርስቲያን ብዙ የእውቀት ዘርፎች አሉ ።እነርሱም ከዜማ ጋራ የተያያዙ ከቅኔ ጋር የተያያዙ እንዲሁም ከመጻሕፍት ትርጓሜ ጋራ የተያያዙ ናቸው ።
፩. ) በዜማ በኩል ለምሳሌ አንድ ሰው የድጓ መምህርየአቋቋም መምህር የዝማሬ መዋስዕት መምህር የቅዳሴ መምህር ሆኖ በመምህርነት ቢመረቅ
፪. ) በቅኔ በኩል ቅኔ ከእነ አገባቡ አውቆ ልዩልዩ የቅኔ መንገዶችን ቀጽሎ በመምህርነት ቢመረቅ
፫. ) በትርጓሜ መጻሕፍት በኩል ከአራቱ ጉባኤያትበአንዱ (በመጻሕፍተ ሐዲሳት ትርጓሜ በሊቃውንት ትርጓሜ መጻሕፍት በብሉያት ትርጓሜ በመጻሕፍተ መነኮሳት ትርጓሜ) የተመረቁመምህራን የሆኑ በተወሰነ ሙያ ላይ የተለየ ጥናት ያደረጉ ባለሙያዎች ስለሆኑ ፒ ኤች ዲ ካለው አንድ ዘመናዊ ምሁር ጋራድካማቸው እና እውቀታቸው ሊነጻጸር ይችላል ። በጠቅላላ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን እውቀት በባለሙያዎች በሚገባ ተጠንቶቢመዛዘን ዋጋው ከላይ ከተጠቀሰው ግምገማ ቢሻል እንጂ አያንስም::

ዘመናዊው ተማሪ ከአብነት ተማሪጋር ሲነጻጸር


  1. ዘመናዊውተማሪ በወላጆቹ ፈቃድ እና የሚፈልገው በወላጆቹ እየተሟላለት የሚማር ሲሆን የአብነት ተማሪ ግን ብዙውን ጊዜ ይሄን እድልአያገኝም ። በመሆኑም የአብነት ተማሪ ከወላጆቹ እርቆ እውቀት ፍለጋ ተሰድዶ የዕለት ምግቡን እየለመነ እየተመገበ ያለ ቤተ ሰብድጋፍ ይማራል ። በእርግጥ አንዳንድ እድለኞች ከወላጆቻቸው ቤት ሳይርቁ የወላጆቻቸው እርዳታ ሳይለያቸው ይማራሉ ። እነዚያ ግንከብዙኃኑ ጋር ሲነጻጸሩ አስር በመቶ እንኳን አይሆኑም ።
  2. ዘመናዊተማሪ ትልቅ ደመወዝ አገኛለሁ ደህና ኑሮ እኖራለሁ በሚል ተስፋ ይማራል ። የአብነት ተማሪ ግን መምህራኑም መናኞች ሀብትንብረት የሌላቸው እንደ ጥንት የግሪክ ፈላስፎች ሀብታቸው ሹመታቸው ደስታቸው እውቀት የሆነ ምስጋናንም እንደ ልብስ ለብሰውየሚኖሩ በመሆናቸው የሚታየው ሥጋዊ ክብር የሥጋም ጥቅም ሳይኖር ይማራል ። ዋና ዓላማውም እግዚአብሔርን ለማገልገል ነው ።
  3. ዘመናዊውተማሪ ስለ ምድራዊው ዓለም በተጨባጭ ነገር ላይ ስለ ተመሠረተው እውቀት እና እስተሳሰብ ያጠናል ። መንፈሳዊው ተማሪ ስለመንፈሳዊው እና በዓይነ ሥጋ ስለማይታየው በእጅም ስለማይዳሰሰው ዓለም እና እግዚአብሔር ያጠናል ።
  4. የዘመናዊውተማሪ እውቀት ከመጽሐፍ ጋር የተያያዘ ነው ። የመንፈሳዊው ተማሪ እውቀት ግን በቃልና በመጽሐፍ ላይ የተመሠረተ ነው ። ከሠላሳእስከ አርባ በመቶ የሚሆነው የቤተ ክርስቲያን ትምህርት በቃል የሚጠና ነው ። በሥራ ላይ የሚውለውም በቃል በየ ጊዜው እየተያዘነው ። በክፉ ዘመን ቅዱሳት መጻሕፍት እንደ አሁኑ በሕትመት ስላልተባዙ ጠላት ያጠፋቸዋል ብለው በመፍራት ብሉያትን እናሐዲሳትን በሙሉ ዘራቸውን እስከ ትርጓሜያቸው በቃል ያጠኑ በአእምሮአቸው የያዙ ሊቃውንት እንደነበሩን ይነገራል ። ይህ የተለየየጥናት ስልት በኢትዮጵያ የአብነት ትምህርት ቤቶች የተለመደ ነው ። ይህም እንደ ዛሬው በቀላሉ መጻሕፍት በማይገኙበት ዘመን ጥቅሙየላቀ ነው ። ዛሬም ቢሆን ይህ ችሎታ የሚደነቅ ነው።
  5. የዘመናዊውተማሪ መምህራኑም የመማሪያ መጻሕፍቱም የሚናገሩት ስለ ዓለም የኑሮ ስልት የዓለምን ሃብት እንዴት በጥቅም ላይ ማዋል እንደሚቻልሰዎችን እንዴት መምራት ሃብትን ንብረትን ንግድን ልዩ ልዩ ተቋማትን እንዴት ማስተዳደር እንደሚቻል ያጠናል ። እንዲሁምየሰዎችን አካላዊና ሥጋዊ ደዌ በሕክምና እንዴት መርዳት እንደሚቻል ሥነ አእምሯዊ ችግሮችን ማኅበራዊ ቀውሶችን እንዴት ተጨባጭ (ሳይንሳዊ)በሆነ መልኩ ብቻ ማስወገድ እንደሚቻል ያጠናል ። ሁሉም ተማሪ በሁሉም ሙያ ስለማይሰለጥን ውስንነቱ እንደተጠበቀ ሆኖ ይህን እናይህን የመሳሰሉትን ሁሉ እንደየ ምርጫው ይማራል ። መንፈሳዊ ተማሪ ደግሞ መምህራኑ መንፈሳውያን መጻሕቱም ቅዱሳት መጻሕፍትናቸው ። መጀመሪያ ከእነሱ የሚያገኘው ትምህርትም መንፈሳዊ ነው ። መንፈሳዊውን ዓለም እና ይህን ዓለም በንጽጽር ያጠናል ። በኃላፊውዓለም ስለ ዘለዓለማዊ ሕይወት ያጠናል ። ያላመኑትን ወደ ሃይማኖት እንዴት እንደሚመልስ ያልዳኑትን እንዴት ወደ እግዚአብሔርእንደሚያደርስ ሥጋዊውን እና መንፈሳዊውን እንዲሁም ስነ ልቦናዊውን እና ማኅበራዊ ቀውስ በወንጌል ትምህርት የጠባይ ለውጥበማምጣት እና በመንፈስ ቅዱስ ረዳትነት እንዴት መለወጥ እንደሚቻል ያጠናል ። ራሱንም በጸሎት ወደ እግዚአብሔር በማቅረብየመፍትሔ ሰው ለመሆን ጥረት ያደርጋል ። ስለዚህ ምንም ሳይኖረው ሁሉ ያለው የተስተካከለ ሥጋዊ ምግብ ሳያገኝ ኃይል የሚሰማውናበመንፈስ ጠንካራ የሆነ ሕይወት አለው ። በጠቅላላ መንፈሳዊው እና ሥጋዊው ትምህርቶች የአቋም የስልትም የእውቀት አተገባበርምልዩነት አላቸው ። አንድ የሚያደርጋቸው ሁሉም ተማሪዎች መሆናቸው እና ሁሉም ለተሻለ ነገር የሚሠሩ እውቀትንም የሚናፍቁለእውቀትም የጊዜ የሕይወት ዋጋ የከፈሉ መሆናቸው ነው ።